Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ እና እስያ የገጠር ልማት ድርጅት በኢትዮጵያ የሚካሄዱ የገጠር ልማት ፕሮጀክቶችን እንደሚደግፍ አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 11 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ እና እስያ የገጠር ልማት ድርጅት በኢትዮጵያ የሚካሄዱ የገጠር ልማት ፕሮጀክቶችን እንደሚደግፍ አስታወቀ።

በሕንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ትዝታ ሙሉጌታ ከአፍሪካ እና እስያ የገጠር ልማት ድርጅት ረዳት ዋና ፀሀፊ ራሚ ኪታይሻት ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸው ወቅት በገጠር ልማት አስተዳደር ጥናት እና በአሳ ሃብት ልማት አስተዳደር ስልጠናዎችና የአቅም ግንባታ ፕሮግራሞችን ማስፋትና ትብብር ማድረግ በሚቻልበት አግባብ ላይ መክረዋል።

አምባሳደር ትዝታ ድርጅቱ ለሀገራት በሚያቀርበው ሥልጠናዎች ኢትዮጵያ በተለያዩ አውደ ጥነት በመሳተፍ እንዲሁም ነጻ የትምህርት ዕድሎችና የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በማግኘት ተጠቃሚ መሆን እንደቻለችና ስለጠናዎቹ ለምታከናውነው የገጠር ልማት ፕሮግራም እንዳገዛት አመላክተዋል።

የአፍሪካ እና እስያ የገጠር ልማት ድርጅት ረዳት ዋና ፀሀፊ ራሚ ኪታይሻት በበኩላቸው፥ በዘርፉ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት ማድነቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

አያይዘውም ድርጅቱ የሚሰጣቸውን እድሎች ለመጠቀም ተጨማሪ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚገባ ጠቅሰው፥ ድርጅቱ ኢትዮጵያ በገጠር ልማት የምታከናውናቸውን ፕሮጀክቶች ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

የአፍሪካ እና እስያ የገጠር ልማት ድርጅት በአፍሪካና እስያ የሚካሄዱ ዘላቂ የገጠር ልማት ፕሮግራሞችን የሚደግፍ ድርጅት ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.