Fana: At a Speed of Life!

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከኢንተርናሽናል ሶላር አሊያንስ ጋር በፀሐይ ኃይል ልማት ዙሪያ በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 11 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከኢንተርናሽናል ሶላር አሊያንስ ጋር በፀሐይ ኃይል ልማት ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሱልጣን ወሊ፥ የጋራ ስምምነቱ በተለይ የገጠሩ ኅብረተሰብ የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ እንዲሆን አጋዥ መሆኑን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይልን ተደራሽ ለማድረግ ከተለያዩ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው የዛሬው ስምምነትም የዚሁ አንድ አካል ነው ብለዋል።

የጋራ ስምምነቱ የኢኮኖሚ ልማትን ለማፋጠንና የመስኖ ልማት ሥራን ውጤታማ ለማድረግ አጋዥ መሆኑም ነው የተገለጸው።

በተለይም በቆላማ አካባቢዎች የሚኖሩ ወገኖች የፀሐይ ኃይል ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል ሲሆን ለአቅም ግንባታ እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ጠቃሚ መሆኑ ተመላክቷል።

የኢንተርናሽናል ሶላር አሊያንስ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አጄይ ማቱር በበኩላቸው፥ በሶላር ኢነርጂ ዘርፍ በኢትዮጵያ ሰፊ ፕሮጀክቶችን በጋራ ለመስራት ፍላጎት መኖሩን ገልጸዋል።

በዚህም የሶላር ፓምፖችን ጨምሮ የፖሊሲ ሂደቶችን በመደገፍ ዙሪያ እንሰራለንም ነው ያሉት።

ኢንተርናሽናል ሶላር አሊያንስ የፀሐይ ብርሃን በስፋት ጥቅም ላይ እንዲውል ለማድረግ ከ100 በላይ ሀገራት በጋር በጋራ የሚሰራ ተቋም መሆኑን ኢዜአ በዘገባው አስታውሷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.