Fana: At a Speed of Life!

የተመረጡ ስራዎችን በማከናወን የማህበረሰቡን የኑሮ ጫና ለማቃለል የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናዋ የተመረጡ ስራዎችን በመስራት እና ውጤት በማምጣት የማህበረሰቡን የኑሮ ጫና ለማቃለል የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
 
በልደታ ክፍለ ከተማ በቀጣይ 60 ቀናት የሚሰሩ ስራዎችን የማስጀመሪያ መርሀሐ ግብር እየተካሄደ ነው።
 
መርሐ ግብሩን በይፋ ያስጀመሩት ከንቲባ አዳነች አቤቤ÷ የሁሉንም ክፍለ ከተሞች ችግር በአንድ ጊዜ መቅረፍ ባይቻልም በተለዩ ክፍለ ከተሞች የተመረጡ ስራዎችን በመስራት እና ውጤት በማምጣት የማህበረሰቡን የኑሮ ጫና ለማቃለል የምናደርገውን ጥረት እንቀጥላለን ብለዋል፡፡
 
የዳቦ አቅርቦት፣ ማዕድ መጋራት እና ምገባን ማስፋፋት፣የከተማ ግብርናን ማስፋፋት፣ አገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል፣ የቤቶች ግንባታ እና እድሳት በትኩረት የሚሰራባቸው ሆነው ተለይተው ወደ ተግባር መገባቱ ተገልጿል።
 
የክፍለ ከተማውን የቤት ችግር የሚያቃልሉ እና 200 አባዎራዎችን የሚይዙት አራት ህንፃዎች ግንባታ፣የዳቦ ፋብሪካ ግንባታ፣ የ200 ቤቶችን አፍርሶ የማደስ እና የምገባ ማዕከል በይፋ የመክፈት መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት የሚካሄድ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
 
ለሚካሄደው የዳቦ ፋብሪካ ግንባታም የመሰረት ድንጋይ በዛሬው ዕለት ተቀምጧል፡፡
 
 
በቅድስት አባተ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.