Fana: At a Speed of Life!

የጋምቤላ ክልል ያለውን የተፈጥሮ ሐብት መሠረት ላደረገ የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ተዘጋጅቷል- አቶ ኡሞድ ኡጁሉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ከፍተኛ አመራሮች ከጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ ሐላፊዎች ጋር በኢንተርፕራይዞች ልማት ዙርያ ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ  ልማት ም/ዋ/ ዳይሬክተር በአቶ ጳውሎስ በርጋ የተመራ ልዑክ ከክልሉ ርዕሠመስተዳደር አቶ ኡሞድ ኡጁሉና ከክልሉ ካቢኔ ጋር ክልሉ ለኢንተርፕራይዝ ልማት ዘርፉ ባለው እምቅ አቅምና በዚህም ሊፈጠር በሚችለው ሐገራዊ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ዙርያ መክሯል፡፡

በመድረኩ ተቋሙ ባቋቋመው የጥናት ቡድን አማካኝነት የተዘጋጀ የክልሉን ምቹ ሁኔታዎችና ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ከነመፍትሔያቸው ያመላከተ ሠነድ የቀረበ ሲሆን÷ በዚህ መነሻነት ሠፊ ውይይት መካሄዱን ከኢንተርፕራይዙ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ርዕሠመስተዳደር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ÷ የጋምቤላ ክልል ያለውን እምቅ ተፈጥሯዊ ሐብት መሠረት ላደረገ የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት መዘጋጀቱን ገልጸው÷ ለዚህም ሠፊ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ  መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.