Fana: At a Speed of Life!

የመጪውን ክረምት የጎርፍ አደጋ ስጋት ለመቋቋም ዝግጅት እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመጪውን ክረምት የጎርፍ አደጋ ስጋት ለመቋቋም ዝግጅት እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲቲዩት አሳሰበ።

የመጪውን ክረምት የጎርፍ አደጋ ስጋት ለመቋቋም ዝግጅት እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመጪውን ክረምት የጎርፍ አደጋ ስጋት ለመቋቋም ዝግጅት እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳሰበ።
ኢንስቲትዩቱ ከሁሉም ክልሎች ከተወጣጡ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ሴክተር አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር መወሰድ ባለባቸው እርምጃዎችና የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ በአዳማ ከተማ እየመከረ ነው።
የሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የአየር ጠባይ አገልግሎት ተመራማሪ ዶክተር አሳምነው ተሾመ፥ የመጪው ክረምት የአየር ሁኔታ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማቶች እንዳይፈትን ተገቢውን የቅድመ ጥንቃቄ ስራ መስራት ይገባል ብለዋል።
በመጪው ክረምት ሊኖር የሚችለውን የጎርፍ አደጋ ስጋት ለመከላከልና ተፅዕኖውን ለመቋቋም ክልሎችና የከተማ መስተዳድሮች ማድረግ ስላለባቸው ጥንቃቄና የቅድመ ዝግጅት ስራ ላይ ለመምከር የተዘጋጀ መድረክ መሆኑ ተገልጿል።
በመጪው ክረምት ወቅት የአየር ሁኔታ መረጃን በትክክል እንዲረዱ ከማድረግ ባለፈ ተጋላጭ የሆኑ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሴክተሮች የጋራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ርብርብ ለማድረግ ነውም ተብሏል፡፡
በተለይ ግብርና፣ ጤና፣ ውሃ፣ አደጋ መከላከል እና ስራ አመራር ተቋማትን ጨምሮ ሌሎች ሴክተሮች በቅንጅትና በትብብር በጉዳዩ ላይ ትኩረት ያስፈልጋል ነው የተባለው።
የፓስፊክ ውቅያኖስ ከመጠን በላይ እየቀዘቀዘ በመምጣቱ የመጪው ክረምት ዝናብ ሁኔታ ከፍተኛ ጎርፍ ሊያስከትል የሚችል መደበኛና ከመደበኛ በላይ የሆነ 85 በመቶ የሀገሪቷ አካባቢ የሚሸፍን ስርጭት እንደሚኖርም መጠቀሱን ኢዜአ ዘግቧል።
የክረምት ወቅትን ተከትሎ ከጤና ስጋት ጋር በተያያዘ ተገቢው ዝግጅትና ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ጥሪ ቀርቧል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.