Fana: At a Speed of Life!

1 ሺህ 167 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት 1ሺህ 167 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ስራ በአጠቃላይ ቁጥራቸው 1 ሺህ 167 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል፡፡
ከተመለሱ ዜጎች ውስጥም 338 ሴቶች 60 ህጻናትና 769 ወንዶች መሆናቸው የታወቀ ሲሆን፥ ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ ተደርጓል፡፡
እስካሁን ድርስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ሥራ ቁጥራቸው ከ 25 ሺህ 800 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.