Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከፍተኛ አመራሮች በከተማዋ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከፍተኛ አመራሮች በከተማዋ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በዛሬው እለት በከተማዋ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሃሳብ አፍላቂነትና የአመራር ሚና የተገነቡና እየተገነቡ ያሉ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
የከተማው አመራር አዲስ ፖለቲካዊ እይታ- አዲስ ሀገራዊ እመርታ በሚል መሪ ቃል የአመራር ስልጠና የጀመረ ሲሆን በስልጠናው መጀመሪያ አመራሩ ፕሮጀክቶችን እንዲጎበኝ መደረጉ በተለይም ጀምሮ የመጨረስ፥ ከፍ ያለ እሳቤን የመላበስና ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ የማድረግን እሳቤ የሚማርበት እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
በጉብኝቱ የተካተቱት ቦታዎች አብርሆት ቤተመፃህፍት፣ ታላቁ ቤተመንግስት መኪና ማቆሚያ፣ የሸገር ቁጥር 2 ፕሮጀክት፣ መስቀል አደባባይ ፕሮጀክት፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሙዚየም እና የማዘጋጃ ቤት እድሳት እንደሚገኙበት ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.