ስፓርት

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ድል ቀንቶታል

By ዮሐንስ ደርበው

May 21, 2022

አዲስ አበባ፣ግንቦት 13፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ24ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ድል ቀንቶታል፡፡

ከሀዋሳ ከተማ ጋር የተጫወተው ኢትዮጵያ ቡና 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል፡፡

የኢትዮጵያ ቡናን የድል ጎሎች አላዛር ሽመልስ እና አማኑኤል ዮሃንስ እንዲሁም ዳግም ተፈራ በራሱ መረብ ላይ ሲያስቆጥር ብሩክ በየነ የሀዋሳ ከተማን ብቸኛ ጎል አስቆጥሯል፡፡

ኢትዮጵያ ቡና ዛሬ ማሸነፉን ተከትሎ በእኩል 37 ነጥብ ከሲዳማ ቡና ጋር 3ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡

ረፋድ ላይ በተደረገ ሌላ መርሃ ግብር አዲስ አበባ ከተማ ከጅማ አባጅፋር አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡