ወሎ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 823 ተማሪዎች አስመረቀ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወሎ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 823 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡
በምርቃ ስነ ስርዓቱ የተማሪ ወላጆችን ጨምሮ የተለያዩ ባድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡
ከተመራቂዎች መካከልም 293ቱ ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በአሸባሪው ህወሓት ከወደመ በኋላ በቅንጅት መልሶ ተቋቁሞ መማር ማስተማር ስራውን ዳግም ጀምሮ ነው ዛሬ ለተማሪዎች ምርቃት የደረሰው፡፡
የዛሬ ተመራቂ ተማሪዎች የሽብር ቡድኑ በፈጸመወ ወረራ ትምህርታቸው ቢስተጓጎልም ቅዳሜና እሁድ ጭምር አካክሰው ቆይታቸውን ያጠናቀቁ ናቸው መባሉን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡