የሀገር ውስጥ ዜና

በሀሰተኛ መረጃና ፕሮፖጋንዳ የዓለምአቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት ለመሳብ የሚደረግ ጥረት ቦታ እንደሌለው መንግስት አስታወቀ

By Feven Bishaw

May 22, 2022

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀሰተኛ መረጃና ፕሮፖጋንዳ የዓለምአቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት ለመሳብ የሚደረግ ጥረት ቦታ የለውም ሲል መንግስት ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ ባወጣው መግለጫ፥ አሸባሪው የትህነግ ቡድን ትክክለኛ ማንነቱን የዓለም ህዘብ እየተመለከተው መምጣቱንና በሀሰት ፕሮፖጋንዳ አሰልፎት የነበረው ድጋፍም መቀዛቀዙን ተከትሎ የዓለምአቀፉን ማህበረሰብ ልብ እገዛበታለሁ ያለውን የምርኮኞችን መፈታት አጀንዳ ለማድረግ እየሞከረ መሆኑን አመልክቷል።