Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ  በተለምዶው  ” ምን አለሽ ተራ” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በአዲስ አበባ  አዲስ ከተማ ክ/ከተማ  መርካቶ አካባቢ  በተለምዶው  ” ምን አለሽ ተራ” ተብሎ በሚጠራው  ቦታ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ፡፡

 

በተከሰተው የእሳት አደጋ የንብረት ውድመት ያጋጠመ ሲሆን÷ የእሳትና ድንገተኛ መከላከል ሰራተኞች፣ የአካባቢው በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችና የፀጥታ ሃይሎች ባደረጉት ርብርብ የከፋ ጉዳት ሳያስከትል በቁጥጥር ስር ለማዋል ተችሏል።

 

የአደጋውን መንስዔና የወደመውን የንብረት መጠን ዝርዝር መረጃ  እየተጣራ መሆኑን ከክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.