Fana: At a Speed of Life!

የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ አመራሮች በክልሉ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በክልሉ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል፡፡

የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች “አዲስ ፖለቲካዊ ዕይታ-አዲስ ሀገራዊ እመርታ” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ከሚገኘው ሥልጠና ጎን ለጎን ነው የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው የጎበኙት፡፡

በጉብኝታቸውም የክልሉ የልህቀት ማዕከልን እና የጠቅላይ አቃቤ ህግ ቢሮን የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል።

በተጨማሪም የዱቄትና የኦክስጅን ፋብሪዎችን፣ ማስ ኢንጅነሪንግን፣ የቂሌ ኤረር ውሃ ማምረቻ ጣቢያንና የአረንጓዴ አሻራ ዝግጅት ያለበትን ደረጃ ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.