Fana: At a Speed of Life!

ከድባጤ እና በቂዶ ሚሊሻዎች ጋር በመተባበር የአሸባሪው ህወሓት ተላላኪዎችን መደምሰሱን የመተከል ኮማንድ ፖስት አስታወቀ

አዲ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመተከል ዞን በድባጤ እና በቂዶ ወረዳዎች የሚገኙ የጉሙዝ የሚሊሻ አባላት ከመከላከያ ሰራዊት ጎን ተሰልፈው ለአሸባሪ ቡድኖች የሚላላኩ ሽፍታዎችን መደምሰሳቸውን የመተከል ኮማንድ ፖስት የተቀናጀ ግብረ ኃይል ተወካይ ኃላፊ ብርጋዴር ጀኔራል ዋለልኝ ታደሰ ተናገሩ፡፡
ብርጋዴር ጀኔራል ዋለልኝ ታደሰ እንደተናገሩት፥ የሚሊሻ አባላቱን ከግል ፍላጎት ወደ ቡድን አንድነት አደረጃጀት በመቀየር በአጭር ጊዜ ውስጥ የአሸባሪው ህወሓት ተላላኪ ሽፍታዎች በመደምሰስ እና የጦር መሳሪያዎችን በመማረክ የቁርጥ ቀን ልጆች መሆናቸውን በተግባር አረጋግጠዋል።
የሚሊሻ አባላቱ ቡድን መሪ ብድኡከም በታሐኒ እንደገለጹት÷ የአሸባሪው ህወሓት ተልዕኮ አስፈፃሚዎችን ሙሉ በሙሉ ለመደምሰስ እና ሕዝቡን ከጥፋት ቡድኖች ለመታደግ ከመከላከያ ሰራዊት ጋር ተቀናጅተን እንሠራለን ብለዋል፡፡
ሌሎች የሚሊሻ አባላት በበኩላቸው÷ ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና ከክልል የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን የኢትዮጵያን ሰላም ለማደፍረስ ቀን ከሌሊት የሚደክሙ የአሸባሪ ኃይሎች ላይ አስፈላጊውን የኃይል እርምጃ ለመውሰድ ተዘጋጅተናል ማለታቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.