ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ሲዳማ ቡና ድል ቀንቶታል

By Meseret Awoke

May 23, 2022

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 15 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና ድል ቀንቶታል።

ከባህር ዳር ከተማ ጋር ጨዋታውን ያደረገው ሲዳማ ቡና ጨዋታውን 3 ለ 1 አሸንፏል።

ጊት ጋትኩት፣ ይገዙ ቦጋለ እና ሀብታሙ ገዛኸኝ የሲዳማን የድል ጎሎች አስቆጥረዋል።

አሊ ሱሌማን ደግሞ የባህር ዳር ከተማን ማስተዛዘኛ ጎል አስቆጥሯል።