Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል በድርቅ የተፈናቀሉ ነዋሪዎችን መልሶ ለማቋቋም ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 15፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል በድርቅ ምክንያት የተፈናቀሉ ነዋሪዎችን መልሶ ለማቋቋም ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ገለፁ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር እስቴቨን አውር እና በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን ተወካይ ዶክተር ማማዱ ዲያን ከተመራ የልኡካን ቡድን ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ በክልሉ የተከሰተው ድርቅ በህዝቡ ላይ ስላደረሰው ጉዳት፣አሁን ላይ በክልሉ ስላለው የድርቁ ሁኔታ እንዲሁም ከተለያዩ ለጋሽ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለህዝቡ የሚያስፈልገውን ድጋፍ ማድረግ ስለሚቻልባቸው ጉዳዮች ምክክር ተደርጓል።

በውይይቱ ላይ የአቶ ሙስጠፌ መሃመድ÷ በክልሉ በተለያዩ አከባቢዎች በርካታ ነዋሪዎች ከመኖሪያ አከባቢዎች መፈናቀላቸውን ጠቁመው በተባበሩት መንግስታትና አለም አቀፍ ሀገራት ድጋፍ ለህዝቡ የተረጋጋ ህይወት እንዲኖሩ ድጋፍ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

የልኡካን ቡድኑ አባላት በቆሎጂ የተፈናቃዮች መጠለያ ማእከል የሚገኙ ተፈናቃዮች ያሉበትን ሁኔታ ይጎበኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከክልሉ መገናኛ ብዙሀን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.