1ሺህ 68 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት 1ሺህ 68 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡
በሦስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳዑዲ አረቢያ የመመለስ ስራ 1ሺህ 68 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ የተቻለ ሲሆን÷ ከእነዚህ ውስጥ አንድ ሕጻንና 1 ሺህ 67 ወንዶች መሆናቸው ታውቋል፡፡
ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ ተደርጓል፡፡
እስካሁን በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ከ 26 ሺህ 868 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡