የሀገር ውስጥ ዜና

የተመድ የሰብአዊ ድጋፍ አስተባባሪ ካትሪን ሱዚ እና የ5 አገራት አምባሳደሮች ጅግጅጋ ገቡ

By Feven Bishaw

May 24, 2022

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ድጋፍ አስተባባሪ ዶክተር ካትሪን ሱዚ ፣ የጣሊያን፣ ጃፓን ፣ ስዊዘርላንድ ፣ ቼክሪፐብሊክ እና ፊንላንድ አምባሳደሮች እና የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት፣ ዩኒሴፍ ፤ ፋኦና አይ ኦ ኤም ኃላፊዎች ረፋዱን ጅግጅጋ ገብተዋል።

የልዑካን ቡድኑ ገራድ ዊል ዋል ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር ፅህፈት ቤት ሀላፊ ዶክተር ሁሴን ሀሺ ቃሲም፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ አያን አብዲና ሌሎች የክልሉ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።