Fana: At a Speed of Life!

14ኛው የዓለም በይነ-ዕምነት ጉባኤ በዶሃ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 14ኛው የዓለም በይነ-ዕምነት ጉባኤ “የጥላቻ ንግግር በሃይማኖታዊና በቅዱሳት መጽሐፍት እይታ” በሚል መሪ ሀሳብ በኳታር ዶሃ መካሄድ ጀመረ፡፡

ኢትዮጵያን በመወከል የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ እና በኳታር የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፈይሰል አሊይ መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ እንደገለጹት÷ በጉባኤው ላይ ምሁራን ከተለያዩ ሀገራት ልምድ በመውሰድ ጥናት ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ጉባኤው በነገው ዕለት የሚቀጥል ሲሆን÷ በማጠናቀቂያው መርሐግብር በጥላቻ ንግግር ዙሪያ ላይ በዓለም የሃይማኖት ተቋማት በሀይማኖቶች ዙሪያ የጋራ መግባባት እና አቋም ላይ ይደርሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.