22ኛው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ድርጅት ጉባኤ በመጪው ሐምሌ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 22ኛው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ድርጅት (በድር ኢትዮጵያ) ጉባኤ ከሀምሌ 8 እስከ 18 ቀን 2014 ዓ.ም ሊካሄድ ነው፡፡
ጉባዔው ከአገራቸው የራቁ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ስለ አገራቸው ያላቸውን ግንዛቤ እንዲያሰፉ ያለመ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ጉባዔው እስላማዊ እሴቶች ለሀገር ሰላም እና እድገት አስተዋጽኦ እንዲኖራቸው የማድረግ ዓላማ ያለው ሲሆን የተለያዩ ሁነቶች እንደሚቀርቡበትም ተገልጿል፡፡
የአገርን በጎ ገጽታ ከማስተዋወቅ አንጻር፣ የቱሪዝም ዘርፍን የማነቃቃት፣ የኢንቨስትመንት አማራጮችን የመጠቆም እና የእውቀት እንዲሁም የቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በትኩረት እንደሚሰራ የፕሮግራሙ አስተባባሪ አቶ መሀመድ ካሳ ገልጸዋል፡፡
በሜሮን ሙሉጌታ