Fana: At a Speed of Life!

በ2030 የህፃናትን መቀንጨር ዜሮ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 16፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2030 የህፃናትን መቀንጨር ዜሮ ለማድረግ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በሰቆጣ ቃል ኪዳን ላይ ለደቡብ ክልል ለባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጃ ዱጉማ እንደተናገሩት የህፃናትን መቀንጨር በ2030 ዜሮ ለማድረግ የ15 አመት እቅድ ተይዞ እየተሰራ ነው።

በሀገሪቱ በ37 ወረዳዎች የሚታየውን የልጅነት የምግብ እጥረት ችግር ለመፍታት የሰቆጣ ቃል ኪዳን ተግባራዊ መደረጉንም ገልጸዋል።
በአገር አቀፍ ደረጃ 37 በመቶ የሚሆኑ ህጻናት የዚህ ችግር ተጠቂ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ በበኩላቸው አመራሩ ህብረተሰቡን በማሳተፍ የድርሻውን እንዲወጣ ጠይቀዋል።

በጅብሪል ሁሴን እና በማቱሳላ ማቴዎስ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.