Fana: At a Speed of Life!

የአዋሽ ወንዝ የሚያደርሰውን የጎርፍ አደጋ ለመከላከል የተጀመረው የግንባታ ስራ በበጀት እጥረት አልተጠናቀቀም ተባለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በክረምት ወራት የአዋሽ ወንዝ በየዓመቱ የሚያደረሰውን የጎርፍ አደጋ ለመከላካል በ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር የተጀመረ የግንባታ ስራ ዛሬም እንዳልተጠናቀቀ ተገለጸ።

የግንባታ ስራው ካልተጠናቀቀ በአፋር እና በኦሮሚያ ክልሎች ወንዙ በየዓመቱ የሚያደርሰው አደጋ ዘንድሮም ሊፈጥር እንደሚችል የክልሎቹ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽንና ቡሳ ጎኖፋ የስራ ኃላፊዎች ስጋታቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል።

የፌዴራል ውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር በበኩሉ ፥ በበጀት እጥረት የተቋረጠው የግንባታ ስራ እንዲጠናቀቅ የተመደበው በጀት በቶሎ እንዲለቀቅ በድጋሚ ለተፋሰሱ ምክር ቤት ጥያቄው ቀርቦ በመጠባበቅ ላይ እንደሆነ አሰታውቋል።

አዋሽ ወንዝ በየዓመቱ በአፋርና በምስራቅ ኦሮሚያ እንዲሁም በደቡብ ክልሎች በሰው ህይውትና በንብረት ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ከፍተኛ ነው።

በዚህም የብዙሃኑ ነዋሪዎች የቅሬታ ምን ሆኖ በመቆየቱ ከተጎጂዎች የምሬት ድምጾች ይደመጣሉ።

በአፋር ክልል ይህን አደጋ ለመከላካል እንዲሁም የሚያሰከተለወን ጉዳት ለመቀነስ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እንዲሁም በክልሉ የውሃ እና ኢነርጂ ቢሮ የግንባታ ስራዎች ውል ተገብተው የተጀመሩት ፕሮጀክቶች በበጀት እጥረት አልተጠናቀቁም።

የክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ ሺማ እንደገለጹት ፥ ባለፉት ጊዜያት በነበረው የህልውና ዘመቻ ምክንያት ለዚህ ጉዳይ የተበጀተው በጀት እንዲዞር ተደርጓል።

በክልሉ ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች ዝናብ ዘንቦ በተለይ አዋሽ ወንዝ በሚያልፈባቸው አካባቢዎች የጎርፍ አደጋ እንዳያደረሰ በአካባቢውን ነዋሪዎቸ ጥንቃቄ እንዲያደረጉ የግንዛቤ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የክልሉ ቡሳ ጎኖፋ ኃላፊ አቶ ሙስጣፋ ከድር ለፋና ብሮድካሰቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

በክልሉ የአዋሽ ወንዝ ሙላት ጉዳት እንዳያደርሰ የተለያዩ የጎርፍ ማስወገጃ ስራዎች የተጀመሩ ቢሆንም፥ በበጀት እጥረት ባለመጠናቀቃቸው የአዋሽ ወንዝ በሚሞላ ጊዜ የጎርፍ አደጋ ጉዳት ያደርሳል የሚል ክፍተኛ ስጋት እንዳላቸው ይናገራሉ።

ለስራው የተፈቀደው ብር እንዲለቀቅ በድጋሜ ጥያቄ አቅርበው ምላሽ እየተጠባበቁ እንደሆነ የነገሩን የፌዴራል የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ሀብታሙ ኢተፋ ናቸው።

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት ሚኒስትሩ ፥ እስካሁን በጀቱ ባለመለቀቁ ውል ተዋውለው ሰራዎችን መስራት እንዳልተቻለ ጠቅሰዋል።

ለ2013 ከተፈቀደው በጀት ግማሹም ቢሆን ተለቆ የክረምት ጊዜው ደረሶ ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት ስራዎች እንዲሰሩ ማደረግ እንደሚገባም ሚኒስተሩ አሳስበዋል።

ሆኖም ግን የጎርፍ አደጋው የሚከሰትባቸው ጊዜያር ከመድረሳቸው በፊትና የተባለው በጀትም እስከሚለቀቅ ድረስ ክልሎች ሌሎች አማራጭ ስራዎችን እያከናወኑ ሊጠባበቁ ይገባልም ብለዋል ሚኒስትሩ።

በሲሳይ ጌትነት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.