የሀገር ውስጥ ዜና

የሲዳማ  ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ልዑካን  በክልሉ የሚገኙ የኢንቨስትመንት ልማት እንቅስቃሴዎችን ጎበኘ

By Feven Bishaw

May 25, 2022

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ  ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ልዑካን በክልሉ የሚገኙ የኢንቨስትመንት ልማት እንቅስቃሴዎችን እና መሰረተ ልማቶችን ጎብኝቷል፡፡

በጉብኝቱ በዘርፉ ካሉ የኢንቨስትመንት መሰረተ ልማቶች አንዱ የሆነውን የይርጋለም የተቀናጀ አግሮ ኢንደስትሪ ፓርክ የተመለከቱ ሲሆን÷በዚህም በፓርኩ ውስጥ እየሰሩ ያሉ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ጎብኝተዋል፡፡