ዓለምአቀፋዊ ዜና

በቴክሳስ የ18 ዓመት ተጠርጣሪ በተኩስ እሩምታ 19 ህጻናት እና 2 ጎልማሶችን ገደለ

By Feven Bishaw

May 25, 2022

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ደቡብ ቴክሳስ በሚገኝ አንድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በደረሰ ጥቃት 19 ህጻናት እና ሁለት ጎልማሶች ተገደሉ፡፡

የ18 ዓመት ተጠርጣሪ ወጣት ከሰባት እስከ 10 ዓመት ዕድሜ ያላቸውን ሕፃናት በሚያስተምር ሮብ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ በከፈተው የተኩስ እሩምታ ነው የ19 ህጻናት ተማሪዎችን እና የ2 ጎልማሶች ህይወትን የቀጠፈው።