ዓለምአቀፋዊ ዜና

ዴኒስ ሽሚጋል የዩክሬን ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተመረጡ

By Tibebu Kebede

March 05, 2020

አዲስ አበባ ፣የካቲት 26 ፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የዩክሬን ፓርላማ ዴኒስ ሽሚጋልን የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ መረጠ።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኦሌክሲይ ሆንቻሩክ በፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ ጥያቄ ስልጣን ለቀዋል።

ፕሬዚዳንቱ ፓርላማው ሽሚጋልን በጠቅላይ ሚኒስትርነት እንዲመርጥላቸው ጠይቀዋል።

የፓርላማ አባላቱም ሽሚጋል ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ በአብላጫ ድምጽ መርጧቸዋል።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ፕሬዚዳንት ዜሌንሲኪ የሚከተሉትን የኢኮኖሚ ፖሊሲ “ኋላ ቀር” በሚል ተችተውታል።

አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የኦሌክሲይ ሁንቻሩክ ምክትል እንደነበሩ ይታወሳል።

ምንጭ፦ ዩናይትድ ፕረስ ኢንተርናሽናል

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision