Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ከ500 ሄክታር በላይ ሰብል በተምች ጉዳት ደረሰበት

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ተምች በደቡብ ምዕራብ ሕዝቦች ክልል ከ500 ሄክታር ላይ ሰብል ላይ ጉዳት ማድረሱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡
የአፍሪካ ተምች እስካሁን በክልሉ ከ500 በላይ ሄክታር ላይ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን፥ ህብረተሰቡ ከዚህ ቀደም በባህላዊ መንገድ ይከላከልበት የነበረውን ልምድ አጠናክሮ እንዲቀጥል ቢሮው አሳስቧል ።
ይህ አደገኛ ተምች በክልሉ ሰብል አብቃይ ዞኖች በስፋት መከሰቱን የገለጸው ቢሮው÷ ተምቹ የሚያስከትለውን ጉዳት በመረዳት መንግስት የመከላከሉን ስራ በስፋት እያከናወነ መሆኑን አብራርቷል፡፡
ተምቹን ከወዲሁ መከላከል ካልተቻለ ጉዳቱ የከፋ ስለሚሆን ህብረተሰቡ የቤተሰብ ጉልበት አደራጅቶ ከመንግስት ጎን በመሆን በእጅ በመልቅም፣ በመጨፍለቅ፣ የማሳውን ውስጥና ዙሪያ በማጽዳትና በየቀኑ ማሳው ላይ ክትትል በማድረግ የመከላከል ስራው ላይ እንዲሳተፍ ቢሮው ጥሪ ማቅረቡን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.