Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በዋግኽምራ ለ19 ሺህ 500 ተፈናቃይ ወገኖች ሰብአዊ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ሁለት ሣምንታት በዋግኽምራ ዞን በዝቋላ ወረዳ ለሚገኙ 19 ሺህ 500 ተፈናቃይ ወገኖች ሰብአዊ ድጋፍ ማድረጉን ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታወቀ፡፡
ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በዋግ ኽምራ ዞን ዝቋላ ወረዳ ለሚገኙ 3 ሺህ 250 አባወራዎች ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል።
የተደረገው የምግብ ድጋፍ ሩዝ፣ ምስር፣ ዘይትና ጨውን ጨምሮ የተለያዩ ሰብአዊ ድጋፎችን ያካተተ መሆኑንም ነው የገለጸው።
ድጋፉም በአካባቢው የሚገኙ 19 ሺህ 500 ተፈናቃዮችን ተጠቃሚ ያደርጋል መባሉን ከዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.