ምዕራባውያን ሩሲያን ከዓለም ኢኮኖሚ ለማግለል የሚያደርጉት ጥረት አይሳካም – ፕሬዚዳንት ፑቲን
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ በምዕራባውያኑ ተፅዕኖ ከዓለም አቀፉ የኢኮኖሚ መድረክ ለቃ እንደማትወጣ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን አስታወቁ ።
ፕሬዚዳንት ፑቲን በበይነ መረብ በተካሄደው የአውሮፓ እና እስያ ሀገራት የኢኮኖሚ ፎረም ላይ ባደረጉት ንግግር፥ ሩሲያን በማዕቀቦች ለመጉዳት እና ለማዳከም የሚሹ ሀገራት እንደማይሳካላቸው ይወቁት ፤ ይልቁንም የሚጎዱት እራሳቸውን ነው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ፑቲን “ማዕቀቦቹ በአንዳንድ ምክንያቶች እንዲያውም አጠንክረውናል” ማለታቸውን አር ቲ ኒውስ ዘግቧል፡፡
ሀገራት ከእኛ ተሞክሮ ልምድ ወስደው በየትኛውም ሀገር ላይ ጥገኛ ያልሆነ የኢኮኖሚ ፖሊሲ መቅረፅ እና ነጻነታቸውን ማወጅ አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡