Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ ወለጋ ዞን ስሬ ከተማ በእሳት አደጋ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ሲቡ ስሬ ወረዳ ስሬ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል።

በእሳት አደጋው በ15 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የሲቡ ስሬ ወረዳ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

በአደጋው ጉዳት ከደረሰባቸው ሰዎች ውስጥ 3 ሰዎች ለህክምና ወደ አዲስ አበባ ሪፈር የተደረጉ ሲሆን፥ 2 ሰዎች ደግሞ ወደ ነቀምቴ ሆስፒታል እንዲሁም ቀሪዎቹ 10 ሰዎች ደግሞ በስሬ ሆስፒታል ህክምና እየተከታተሉ ይገኛሉ ተብሏል።

በተጨማሪም በእሳት አደጋው 15 የሚሆኑ የአልባሳት፣ የጫማ፣ የሞባይል ስልክ ቤቶች እንዲሁም የሸቀጣ ሸቀጥ መደብሮችን ጨምሮ መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል።

ቃጠሎ በደረሰባቸው በንግድ እና የመኖሪያ ቤቶች ውስጥ የነበሩ ንብረቶችም ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ተነግሯል።

የእሳት አደጋው መንስኤ እስካሁን እየተጣራ መሆኑን ከወረዳው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.