Fana: At a Speed of Life!

የመጀመሪያው ከተማ-አቀፍ የኅብረት ስራ ኤግዚቢሽን፣ ባዛር እና ሲምፖዚዬም ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመጀመሪያው ከተማ-አቀፍ የኅብረት ስራ ኤግዚቢሽን፣ ባዛር እና ሲምፖዚዬም በዛሬው ዕለት በይፋ ተከፍቷል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ህብረት ስራ ኤጀንሲ የተዘጋጀውን ከተማ አቀፍ የህብረት ስራ ኤግዚቪሽን፣ ባዛር እና ሲምፖዚዬም የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በይፋ አስጀምረዋል፡፡
ኤግዚቢሽንእና ባዛሩ ” የኅብረት ሥራ ግብይት ለሰላምና ለተረጋጋ የግብይት ሥርዓት!” በሚል መሪ ቃል ከግንቦት 18 እስከ 21 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ነው የሚካሄደው፡፡
ከተማ አስተዳደሩ በከተማው ያለውን የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት ከተማ አስተዳደሩ ከተዘዋዋሪ ፈንድ በተጨማሪ የእሁድ ገበያን በማስፋፋት ላይ እንደሚገኝም አቶ ጃንጥራር ተናግረዋል፡፡
በይፋ የተከፈተው የመጀመሪያውን ከተማ አቀፍ የህብረት ስራ ኤግዚቪሽን፣ባዛር እና ሲምፖዚዬም የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት ጉልህ ሚና እንደሚጫዎትን ጠቁመዋል፡፡
በኤግዚቢሽንና ባዛሩ የቀረቡ የግብርና ምርቶች እንደ ጤፍ፣ ፣ ሽንብራ፣ ባቄላ፣ አተር፣ በቆሎ፣ ቡና፣ የተለያዩ ቅመማ ቅመሞች፣ ዛላ በርበሬ፣ ማር፣ እና የተለያዩ አትክልቶች እና ፍራፍሬዎች እንዲሁም የኢንዱስትሪ ምርቶችም ተጎብኝተዋል፡፡
በኤግዚቢሽንና ባዛሩ ከኦሮሚያ፣ አማራ፣ ደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ ሲዳማ፣ እና በቤንሻንጉል-ጉሙዝ የተውጣጡ 23 የኅብረት ስራ ማኀበራት መሳተፋቸውንም ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.