በትራፊክ አደጋ የእናትና ልጅ ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ሸዋ ዞን ጣርማ በር ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የእናትና ልጅ ህይወት ማለፉን የወረዳው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
አደጋው አስፍቸው ቀበሌ ልዩ ቦታው ጭራሜዳ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ የደረሰ መሆኑን የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ሸዋ ታጠቅ ኃይለሥላሴ ተናግረዋል።
ከኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ባቲ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረ አምቡላንስ ተሽከርካሪ መንገድ ዳር መኪና በመጠበቅ ላይ የነበሩ እናትና ልጅ ገጭቶ ህይወታቸው ማለፉንም ነው የተናገሩት።
ዋና ኢንስፔክተሩ አያይዘውም በአደጋው ሁለት ሰዎች ላይ ቀላል አደጋ ደርሷል ብለዋል፡፡
አሽከርካሪው በቁጥጥር ስር መዋሉ እና የአደጋው መንስኤም እየተጣራ መሆኑን የጣርማ በር ወረዳ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።