የሀገር ውስጥ ዜና

የአፍሪካ ኅብረት ልዩ የመሪዎች ጉባዔ መካሄድ ጀመረ

By Alemayehu Geremew

May 27, 2022

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ኅብረት ልዩ የመሪዎች ጉባዔ በኢኳቶሪያል ጊኒ ዋና ከተማ ማላቦ እየተካሄደ ነው።

ጉባዔው በሰብአዊ እርዳታና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም ፀረ ሽብር ጉዳዮች ላይ እና ኢ-ሕገ መንግሥታዊ በሆነ መንገድ ሥልጣን ለመያዝ የሚደረጉ ጥረቶችን መከላከል በሚቻልበት አግባብ ላይ ይመክራል ተብሎም ይጠበቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጉባኤው ለመሳተፍ በትናንትናው እለት ማላቦ መግባታቸው የሚታወስ ነው።