Fana: At a Speed of Life!

በዛሬው እለት 1ሺህ 166 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 1ሺህ 166 ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕልት ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ከተመላሾቹ ውስጥ 169 የሚሆኑት ሴቶች ሲሆኑ÷133ቱ ደግሞ ህጻናትና መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ መደረጉን ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
እስካሁን ድረስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ቁጥራቸው ከ29 ሺህ 120 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉ ነው የተገለጸው፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.