በፍላቂት ገረገራ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ወሎ ዞን በፍላቂት ገረገራ ከተማ አስተዳደር 02 ገረገራ ልዩ ቦታው ሸዋበር በተባለ አካባቢ በፍላቂት ገረገራ ከተማ አስተዳደር በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
በአካባቢው ዛሬ ከጠዋቱ በግምት 2 ስዓት ከጋይንት ወደ ጋሸና ሲጓዝ የነበረ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ከ023 ሃና መኳት ቀበሌ ወደ ገረገራ ከሚጓዝ ባጃጅ ጋር ተጋጭቶ በባጃጁ ተሳፍረው ከነበሩ ሰዋች መካከል የ3 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ አልፏል፡፡
በሶስት ሰዎች ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ከመቄት ከተማ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።
ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዋች በሸደሆ መቄት የመጀመርያ ደረጃ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደገላቸው መሆኑን ከሆስፒታሉ የተገኘው መረጃ ያመላክታል ።
በንብረት ላይም ከባድ ጉዳት የደረሰ መሆኑና የአደጋው መንስኤ በፖሊስ እየተጣራ መሆኑን የፍላቂት ገረገራ ከተማ አስተዳድር ፖሊስ ጽ/ቤት የግድያና ዘረፋ ልዩ ልዩ ወንጀሎች ንዑስ ክፍል ኃላፊ ምክትል ሳጅን ሻንበል በለጠ ገልጸዋል ።