የሀገር ውስጥ ዜና

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ

By Feven Bishaw

May 28, 2022

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ስኬት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

ከዓለም ባንክ የተውጣጣ የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ከሚተገብሩ መስሪያ ቤቶች ጋር በፕሮጀክቱ ትግበራ ዙሪያ መክሯል።

በቀጣይ የመሰረተ ልማት ግንባታ እና ተጨማሪ አዳዲስ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መወያየቱንም ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የባንኩ የአይሲቲ ፖሊሲ መሪ እና የኢትዮጵያን የዲጂታል ፋውንዴሽን ፕሮጀክት የሚከታተሉት ዶክተር ቲም ኬሊ÷ የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ስኬት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ÷ በፕሮጀክቱ አፈፃፀም ላይ ማብራራያ የሰጡ ሲሆን÷ የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም እንዲሳካ እያደረገ ላለው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡