“ከወንድሜ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገናል” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ እንደወትሮው ሁሉ ከኬንያው ፕሬዚዳንት ከወንድሜ ኡሁሩ ኬንያታ ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገናል” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።
የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር በሁለትሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በሁለትዮሽ የሰላምና ልማት ጉዳዮች እንዲሁም በባለብዙ ወገን በቀጠናው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡
ውይይታቸው ውጤታማ እንደነበር ገልፀው፥ ለተደረገላቸው ወንድማዊ አቀባበልም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ምስጋና አቅርበዋል።