የሀገር ውስጥ ዜና

የካራማራ ድል 42ኛ ዓመት ተከበረ

By Tibebu Kebede

March 05, 2020

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊያው መሪ ዚያድባሬ ጦር በ1969 ዓ.ም ኢትዮጵያን ለመውረር የሞከረበትና ድል የተደረገበት የካራማራ ድል 42ኛ ዓመት በዛሬው ዕለት ተከበረ።

በዓሉ አዲስ አበባ በሚገኘው የኢትዮ ኩባ የወዳጅነት ፓርክ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።