የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ የዓለም ጤና ድርጅት ተተኪ የስራ አስፈጻሚ ቦርድ አባል ሆና ተመረጠች

By Feven Bishaw

May 28, 2022

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጀኔቫ ሲዊዘርላንድ እየተካሄደ ባለው 75ኛው የአለም ጤና ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ የአለም ጤና ድርጅት ተተኪ የስራ አስፈጻሚ ቦርድ አባል በመሆን ተመርጣለች።

ከአፍሪካ ኢትዮጵያና ሴኔጋል ናቸው ተተኪ የስራ አስፈጻሚ ቦርድ አባል በመሆን የተመረጡት፡፡