Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ከኮካ ኮላ ኩባንያ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከኮካ ኮላ ኩባንያ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በኮካ ኮላ ሊቀ መንበር ጄምስ ኩይንሲ የተመራ ቡድንን በዛሬው እለት በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በዚሁ ወቅት የኮካ ኮላ ልዑካን ኩባንያው በኢትዮጵያ ውስጥ እየሰራ ያለውን ስራ እና ለማስፋፋት የጀመሩትን ስራ አቅርበዋል።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴም፥ ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ዝግጁ መሆኗን ለልዑካን ቡድኑ ገለፃ ማድረጋቸውን የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ባወጣው መረጃ አመላክቷል።

የኮካ ኮላ ኩባንያ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ቀደም ብለው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር መወያየታቸው ይታወሳል።

ኮካ ኮላ በኢትዮጵያ ስራ ከጀመረ 60 ዓመታትን አስቆጥሯል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.