የሰኔ ወር የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም የቤንዚን፣ የናፍጣ እና የኬሮሲን የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በግንቦት ወር ሲሸጥበት በነበረው እንደሚቀጥል የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ነገር ግን የአውሮፕላን ነዳጅ፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣ እና የከባድ ጥቁር ናፍጣ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በዓለም አቀፍ ዋጋ ተሰልቶ የመጣው ልዩነት ሙሉ በሙሉ ወደ ተጠቃሚው እንዲተላለፍ ተወስኗል ነው የተባለው፡፡