Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ለሚገኙ 8 ሺህ ተፈናቃዮች ሰብአዊ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ለሚገኙ 8 ሺህ ተፈናቃዮች ሰብአዊ ድጋፍ ተደረገ።

ድጋፉን ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ እና የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን በጋራ ያደረጉት ነው።

በዚህም ስንዴ፣ ዘይት፣ ጨው፣ ምስርን ጨምሮ ጥራጥሬ ድጋፍ እንደተደረገላቸው ከተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ከዚህ ቀደም በትግራይና አማራ ክልል የተለያዩ ሰብአዊ ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.