Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ባቢሌ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞን ባቢሌ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።

አደጋው ከሀረር ወደ ጅግጅጋ ይጓዝ የነበረ ሚኒባስ ከባቢሌ ከተማ ወደ ገመቹ ቀበሌ እየተጓዘ ከነበረ ባለ ሦስት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ የደረሰ መሆኑን የዞኑ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

በኮሚሽኑ የኮሙዩኒኬሽን ዲቪዥን ኃላፊ ኮማንድር ስዩም ደገፋ እንደገለጹት፥ በአደጋው የባጃጅ አሽከርካሪውን ጨምሮ የስድስት ሰዎች ህይወት አልፏል።

በተጨማሪም በአራት ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ነው የገለጹት።

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑን የገለፁት ኮማንደር ስዩም፥ የሚኒባስ አሽከርካሪው አደጋው ከደረሰ በኋላ ከአካባቢው መሰወሩን ተናግረዋል።

በተሾመ ኃይሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.