Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ማህሌት ሃይሉ ከአውሮፓ ህብረት አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 26 ፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ)በኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቋሚ ተጠሪ አምባሳደር ማህሌት ሃይሉ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በአሁኑ ወቀት በዓለም አቀፍ ደረጅ እየተስፋፋ የመጣውን የጦር መሳሪያ ዝውውር ከመቀነስ አንፃር በአውሮፓ ህብረት እየተወሰዱ ባሉ እርምጃዎች ዙሪያ መክረዋል።

እንዲሁም የጾታ እኩልነት፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና ሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች ለዓለምአቀፍ ሰላም እና መረጋጋት ያላቸውን አዎንታዊ ሚና በተመለከተ ተወያይተዋል።

የአውሮፓ ህብረት የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ተግባራዊ እንዳይደረግ እና እንዳይስፋፋ የተደረሱ ዓለም አቀፍ ስምምነቶች እና የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመቀነስ የተፈረሙ ስምምነቶች ተግባራዊ እንዲሆኑ በትኩረት እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተመላክቷል።

ከዚህ ባለፈም አምባሳደሮች በቀጣይ በህብረቱ ሊተገበሩ በታሰቡ እቅድች ዙሪያ ገላጻ ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያም በዘርፉ የተደረሱ ስምምነቶች ተግባራዊ እንዲሆኑ የምታደርገውን እንቅስቃሴ አጠናክራ እንደምትቀጥል እምነታቸው መሆኑን ገልጸዋል።

አምባሳደር ማህሌት በበኩላቸው ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ ትልቅ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኗን እና በቅርቡ አፍሪካ ከጦር ቀጠና ነጻ ለማድረግ የተደረሰው ስምምነት አንዱ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።

ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ተግባራዊ እንዲደረጉ በዘርፉ የምታበረክተውን አስተዋፅኦ አጠናክራ እንደምትቀጥል አብራርተዋል።

በአሁኑ ወቅት በበርካታ የዓለም ሀገራት እየተስፋፋ ያለውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመግታት በኢትዮጵያ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ በተመለከተም ማብራሪያ ሰጥተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.