ስፓርት

ሉሲዎቹ ነገ ከዛንዚባር አቻቸው ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ

By Feven Bishaw

June 01, 2022

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ነገ 7 ሰዓት ከዛንዚባር አቻው ጋር ጨዋታውን ያደርጋል ፡፡

በሴካፋ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ስፍራው የደረሰው ብሔራዊ ቡድኑ ዛሬ ረፋድ ላይ የመጀመሪያ ልምምዱን አከናውኗል።

በምድብ ሁለት ከታንዛኒያ፣ ዛንዚባር እና ደቡብ ሱዳን ጋር የተደለደለው ቡድኑ የመጀመሪያ ጨዋታውን ነገ 7 ሰዓት ከዛንዚባር አቻው ጋር እንደሚደርግ ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል።