ዓለምአቀፋዊ ዜና

የአፍሪካ ኅብረት እና የአውሮፓ ምክር ቤት አባላት በዩክሬን ጉዳይ ላይ ተወያዩ

By Alemayehu Geremew

June 01, 2022

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ኅብረት እና የአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት አባላት በዩክሬን ጉዳይ ላይ በበይነ-መረብ ተወያይተዋል፡፡

የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀ-መንበር የሴኔጋሉ ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል ÷ ስብሰባቸው በዩክሬን በተከሰተው ግጭት ምክንያት ባጋጠመው የምግብ አቅርቦት ችግር ላይ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

ማኪ ሳል ስብሰባውን ያካሄዱት ዩክሬንና ሩሲያን በጥቂት ሣምንታት ውስጥ ለመጎብኘት ፍላጎት እንዳላቸው ለሀገራቱ ከገለጹ ከቀናት በኋላ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የጉብኝታቸው ትኩረትም ሃገራቱ ወደ አፍሪካ ይልኩት የነበረውን የጥራጥሬ ምርት እንዲቀጥሉ ለማግባባት ያለመ መሆኑን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡