Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ለዩክሬን የምታደርገው የጦር መሳሪያ ድጋፍ ‘በእሳት ላይ ቤነዚን’ እንደመጨመር ነው – ሩሲያ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ለዩክሬን በምትሰጠው የጦር መሳሪያ እርዳታ ‘በእሳት ላይ ቤንዚን’ እየጨመረች ነው ስትል ሩሲያ የአሜሪካን ድርጊት አወገዘች፡፡

 

አሜሪካ ለዩክሬን የተራቀቁ ሚሳኤሎችን ለማቅረብ ማቀዷ ሆን ብላ ግጭቱ ወደ አልተገባ ደረጃ እንዲያድግ መፈለጓን ያሳያል ሲሉ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ተናግረዋል።

 

የሩሲያው ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰርጌይ ርያብኮቭ በበኩላቸው÷ አሜሪካ አዲሶቹን የሚሳኤል ጦር መሳሪያዎች ለዩክሬን ለማቅረብ ማቀዷ ከሩሲያ ጋር ቀጥተኛ ግጭት ውስጥ ሊከት የሚችል አደጋ እንደሚያስከትል ተናግረዋል፡፡

 

የአውሮፓ ኀብረት በቀጣይ ሊያደርገው ያሰበውን የኃይል ማዕቀብ በተመለከተም÷ ማእቀቡ ሩሲያን ጨምሮ ለአውሮፓ ሀገራት፥ ለአሜሪካ እና ለመላው የሃይል ገበያ አሉታዊ ተጽዕኖ መፍጠሩ አይቀርም ብለዋል።

 

በሩሲያ በኩል ጉዳቱን ለመቀነስ የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ ነው ማለታቸውንም ቲአርቲ ዘግቧል፡፡

 

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ትናንት በኒውዮርክ ታይምስ በታተመ ጸሁፍ ላይ፥ አሜሪካ ልህቀት ያላቸው ዘመናዊ የሮኬት መሳሪያዎችን ለዩክሬን ታቀርባለች ማለታቸው የተዘገበ ሲሆን ዋሽንግተን በርካታ የሮኬት ማስወንጨፊያዎችንም ለዩክሬን ለመላክ መስማማቷን በርካታ የዓልም መገናኛ ብዙኃን መዘገባቸው ይታወሳል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.