Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል ከ10 የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ጋር ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል የሲሚንቶ ዋጋ መናር መግታትና መከላከል ያስችለኛል ያለውን ስምምነት ከ10 የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ጋር ተፈራረመ።

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲ እና የፋብሪካዎቹ ተወካዮች ስምምነቱን ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ ፋብሪካዎቹ በሙሉ አቅም ሲሚንቶ  እንዲያመርቱና ምርታቸውን ከሚሸጡላቸው ኤጀንሲዎች ጋር ያላቸውን ውል አቋርጠው ምርታቸውን በአነስተኛና ጥቃቅን ለተደራጁ ማህበራት እንዲያቀርቡ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

ምርት የሚቀርብላቸው 300 ማህበራት ስራ አጥ ወጣቶች፣ የተቸገሩ ወገኖችና በተለያዩ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች መሆናቸው ተነግሯል።

ውላቸው እንዲቋረጥ የተባሉት ኤጀንሲዎች ደላሎችን በሲሚንቶ ሽያጭ ውስጥ እንዲሳተፉ በማድረግ የዋጋ ንረት እንዲከሰት ማድረጋቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመላክታል።

በስምምነቱ መሰረት ፋብሪካዎቹ ሲሚንቶ የሚሸጡት የኦሮሚያ ክልል ባወጣው የዋጋ ተመን የትራንስፖርት ዋጋ ብቻ በመጨመር እንደሆነ ነው የተገለጸው።

የኦሮሚያ ክልል የሲሚንቶን ዋጋ ንረት አስመልክቶ ባደረገው ጥናት መሰረታዊ የሚባሉ ችግሮች መለየታቸው በዚሁ ወቅት ተገልጿል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.