Fana: At a Speed of Life!

የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ዘርፍን ለማነቃቃት አዳዲስ አማራጮችን ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ ነው – የኢንቨስትመንት ኮሚሽን

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ዘርፍን ለማነቃቃት አዳዲስ አማራጮችን ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት በኮሚሽኑ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ዳይሬክተር አቶ አስቻለው ታደሰ እንዳሉት÷ በዘርፉ በኮሮና ቫይረስ ስርጭት እና በሰላምና መረጋጋት እጦት ምክንያት ችግሮች አጋጥመዋል፡፡
በዚህም በዘርፉ አዳዲስ ባለሃብቶችን በሚፈለገው ደረጃ መሳብ ባይቻልም፥ እየተንቀሳቀሱ ያሉትን ለመደገፍ ትኩረት መሰጠቱን አብራርተዋል።
ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማሩት የመሰረተ ልማት እና ሌሎች አስፈላጊ ድጋፎች እንዲመቻቹ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት እንዳሳዩም ነው የተጠቆመው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፥ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን የበለጠ ለማሳደግ አዲስ የፕሮሞሽን እና ማበረታቻ ስትራቴጂዎች ተነድፈው ወደ ተግባር ለመቀየር ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ተገልጿል ።
በበጀት ዓመቱ 9 ወራት ውስጥም ከውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ለማግኘት ከታቀደው 3 ነጥብ 63 ቢሊየን ዶላር ውስጥ 2 ነጥብ 43 ቢሊየን ዶላር ማሳካት መቻሉ ተመላክቷል።
በአወል አበራ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.