Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ እና በቻይና ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ኤጀንሲ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ምክክር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ከቻይና ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ኤጀንሲ ቀጠናዊ ጉዳዮች መምሪያ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዣንግ ሊሁዋ ጋር መክረዋል፡፡

ምክክሩ በኢትዮጵያ እና በቻይና ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ኤጀንሲ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በውይይቱ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ፥ ሁለቱ ሀገራት ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዳላቸው አንስተዋል፡፡

አምባሳደር ተሾመ ቶጋ የቻይና ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ኤጀንሲ የኢትዮጵያን የ10 ዓመታት የልማት ዕቅድ እና ለአዳዲስ እንዲሁም በሂደት ላይ ላሉ የልማት ፕሮጀክቶች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

አምባሳደሩ የቻይና መንግስት ለኢትዮጵያ ላደረገው ሁለንተናዊ የልማትና የሰብዓዊ ድጋፎች በኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ስም አመስግነዋል።

ዣንግ ሊሁዋ በበኩላቸው ፥ ቻይና በሁለቱ ሀገራት መካከል ላለው ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ትኩረት እንደምትሰጥ ነው የተናገሩት።

ከፈረንጆቹ 1970 ጀምሮ በኢትዮጵያና ቻይና መካከል ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደተጀመረ የተመለከተ ሲሆን ከዚያን ወቅት ጀምሮም ቻይና ለኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እና የልማት ሥራዎች ስታከናውን መቆየቷን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.