በጋዛ በደረሰ እሳት አደጋ ዘጠኝ ሰዎች ለህልፈት ተዳረጉ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 27፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋዛ ሰርጥ በዳቦ መጋገሪያ በተነሳ እሳት ዘጠኝ ሰዎች ለህልፈት ተዳረጉ።
በእሳት አደጋው ከሞቱት በተጨማሪ 60 ሰዎች መቁሰላቸውም ነው የተነገረው።
ከእነዚህ ውስጥ 14ቱ በፅኑ የቆሰሉ ሲሆን፥ ለህልፈት ከተዳረጉት ውስጥ ደግሞ ስድስቱ ህፃናት ናቸው ተብሏል።
በዳቦ ቤቱ ውስጥ ለማብሰያነት ከሚያገግሉት ጋዞች በአንደኛው ላይ የተነሳ እሳት ለአደጋው መንስኤ መሆኑም ተነግሯል።
በእሳት አደጋው ሳቢያ በዳቦ ቤቱ አቅራቢያ የሚገኙ መጋዘኖች፣ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች፣ ፋብሪካዎች እና ሱቆች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል ነው የተባለው።
ምንጭ፦ አልጀዚራም