Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ንቅናቄ መድረክ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳ የሚመሩትና ኢትዮጵያ ታምርት በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ንቅናቄ መድረክ በጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ የንቅናቄ መድረኩን ቡታጅራ ከተማ የሚገኘውን ደስታ ጋርመንት ፋብሪካ በመጎብኘት ነው ያስጀመሩት፡፡

በዚህ ወቅት ርዕሰ መስተዳድሩ በግል ባለሀብቶች ጥረት ተገንብቶ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የአልባሳት ፋብሪካ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በማሳደግ ረገድ የድርሻውን እየተወጣ ነው ብለዋል።

ፋብሪካውን ከዚህ ቀደም በጎበኙበት ወቅት የሃይል እጥረት እንደነበረበት ተነስቶ እንደነበር አስታውሰው÷ አሁን ችግርሩን መቅረፍ እንደተቻለ ተናግረዋል።

ፋብሪካው ለወጣቶች የስራ እድል ከመፍጠር አንጻር ሚናው የላቀ መሆኑን እና የፋብሪካውን ማስፋፊያ ለማሳደግ ያጋጠመውን ችግር ለመፍታትጥረት ይደረጋል ብለዋል።

የደስታ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግልማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ እዮብ በቀለ ÷ በአዲስ አበባ እና በቡታጅራ ከተማ በሚገኙ ፋብሪካዎች ከ1ሺህ 300 በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች የስራ እድል መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡

የጨርቃ ጨርቅ ምርቶችን ወደ አሜሪካ እና የአውሮፖ አገራት ኤክስፖርት በማድረግ ላይ መሆናቸውንም ነው የጠቆሙት።

ከጨርቃጨርቅ ምርት በዓመት ወደ 4 ሚሊየን የሚጠጋ የአሜሪካን ዶላር የውጪ ምንዛሬ ማግኘት እንደተቻለ የገለጹት ስራ አስኪያጁ÷ ፋብሪካው በሙሉ አቅም ማምረት ሲጀምር በዓመት እስከ 10 ሚሊየን ዶላር ማግኘት እንደሚቻል አብራርተዋል።

በንቅናቄ መድረኩ በክልሉ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች በተለይም በኢንዱስትሪው ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶች በስራ ሂደት እያጋጠሟቸው ባሉ ችግሮች ዙሪያ ውይይት ተደርጎ የመፍትሄ አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ ይጠበቃል ።

በመርሃ ግብር ፌደራል ፣ የክልልና የዞን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ፣ ባለሃብቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.